Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

6ኛ እርምጃ፦ ዘሮችን መዝራትና የተጠቀምንባቸዉን መተካት

በጊዜ ሂደት የዘር ባንኩ ምርታቸዉ ለቀነሰባቸዉና ለተጎዳባቸዉ ገበሬዎች ዘር ይሰጣል፤ በዚህ ጊዜ ዘሮችን መተካት ያስፈልጋል፡፡ ዘሮቹም በራሳቸዉ መብቀል ከጀመሩም መተካት ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህም በየጊዜዉ ዘሮቹን መከታተል ያስፈልጋል፡፡

ዘሮች ጤናማ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ በረጠበ ጋዜጣ ላይ ዘሮቹን ያስቀምጡ ከዚያም ጋዜጣዉን ይጠቅልሉትና ሞቃታማና ፀሐያማ በሆነ አካባቢ ያስቀምጡት፡፡ ጋዜጣዉ በትንሹ እርጥበታማ መሆኑት ያረጋግጡ፡፡ ከ6 እስከ 12 ቀናት ዉስጥ ዘሮቹ መብቀል ይጀምራሉ፡፡ ያልበቀሉት ዘሮች ሞተዋል ማለት ነዉ በመሆኑም ለእንስሳት መኖነት ሊያገለግል ይችላል፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ዘሮች ከበቀሉ ያስቀመጡት ዘሮች ጤናማ ናቸዉ ማለት ነዉ፡፡ በመሆኑም ተጨማሪ አያስፈልጎትም፡፡ 

ያስቀመጡትን ዘሮች ለመዝራት ሲፈልጉ የሚከተሉትን ነገሮች ያስታዉሱ፦

ለመዝራት የመረጡት ቦታ ዘሩ መጀመሪያ ከመጣበት በታ ጋር ተመሳሳይ ቢሆን ይመረጣል፡፡

ዘሩን በሚዘሩበት ወቅት በእርሻዉ የተለያየ በታ ይዝሩት፤ ለመጪዉ ጊዜ ጥሩ የዘር ምንጭ ለማግኘት ያስችለናል፡፡

መጀመሪያዉኑ ካልተቀላቀሉ በስተቀር ከተለያዩ ዝርያዎች ጋር በመቀላቀል አይዝሩ፡፡

 

 

0
No votes yet
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation