Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

1ኛ እርምጃ፦ ሰራተኞችን ያደራጁ

በመጀመሪያ ደረጃ የአካባቢ የዘር ባንክን ለማቋቋም ታታሪ የሆኑ አቃጆችና ሰራተኞች ያስፈልጉታል፡፡ በመሆኑም ሰራተኞቹን በጥንቃቄ መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ገበሬዎች ወይም የተለያዩ የሕብረተሰቡ አካላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አካባቢያዊ ድርጅቶችም የዚህ አካል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህም ዉሳኔ ለአካባቢዉ ነዎሪዎች የሚተዉ ነዉ፡፡

የመጀመሪያዉና እጅግ አስፈላጊዉ ነገር ሁሉም በስራዉ የሚሳተፉት ሰዎች ምን ያህል ስራ እንደሚጠበቅባቸዉ በሚገባ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በባንኩ ዉስጥ ዉስን ስራዎች ሊሰጣቸዉ ይችላል፡፡ ማንኛዉም ገበሬ ሊነግራችሁ እንደሚችለዉ ዘር መሰብሰብ፣ ዘር ማዘጋጀትና ማስቀመጥ አመቱን ሙሉ የሚከናወን ስራ ነዉ፡፡ በመሆኑም ከፍተኛ ስራና ተነሳሽነት ይጠይቃል፡፡

ሰዎቹ በትጋት ለመስራት ከወሰኑ የሚቀጥለዉ እርምጃ የሚሆነዉ የሚሰበሰቡትን የዘር አይነቶች መወሰን ነዉ፡፡ ሁሉንም አይነት በአካባቢዉ የሚገኙ የዘር አይነቶችን ማካተት አይዘንጉ፤ ስማቸዉንም ይመዝግቡ፡፡ የተለያዩ የዐዝርዕት፣ የዛፍ፣ የመድሓኒትና የምግብ ተክሎች ዝርያዎችን ያካቱ፡፡

 

0
No votes yet
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation