Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

የወተትና የወተት ተዋፅኦ አመራረት አያያዝና አጠቃቀም

ባህላዊ የወተትና የወተት ተዋፅኦ አደረጃጀት የተመሰረተው በረጋ ወተት ወይም በእርጎ ላይ ነው። ይህም የሆነበት በርካታ ምክንያቶች አሉት፡-

ለትኩስ ወተት ገበያ አለመኖር

ወተት የሚረጋ ስለሆነ ትኩስ ወተትን ለማደራጀት አማራጭ ቴክኖሎጂ አለመኖር

የረጋ ወተት ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ

ለባህላዊ መናጫ ተስማሚ መሆኑ

ቅቤ ሳይበላሽ ለረጅም መንገድ ማጓጓዝ ስለሚቻል

ቅቤን ለገቢ ምንጭነት ለመጠቀምና አሬራውን ለቤተሰብ ፍጆታ ለማዋል

ቅቤና አይብ በባህላዊ አመጋገብ በጣም ተፈላጊ መሆን

ወተት በጥሬው፣ በእርጎ ፣ በቅቤ፣ በአሬራ ፣ በአጓትና በአይብ መልክ ጥቅም ላይ ይውላል። በወተት ልማትና ኢንዱስትሪ ባደጉ አገሮች ወተትን በብዛት የማምረት፣ የማከማቸት፣ የማቀነባበርና የማጓጓዝ ስራ በከፍተኛ ቴክኖሎጂ ተደግፎ ጥቅም ላይ ይውላል።

በኢትዮጵያ ከ1950 ጀምሮ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተቋቋሙ ዘመናዊ የመንግስት፣ የግለሰብ የህብረት ስራ ማህበራትና የወተት ከብት አርቢዎች፣ የወተት አመራረትና አዘገጃጀት የሚያገለግሉ ፋብሪካዎች ተከፍተዋል።

 

1.8
አማካይ: 1.8 (5 votes)
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation