Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

የወተት እንስሳት ዓይነትና ዝርያ ስርጭት

የወተት ተዋፅኦ የሚመረተው በተለያዩ ስነ ምህዳርና ቀጠናዎች ከዳልጋ ከብት፣ ከፍየል፣ ከግመልና ከበግ ነው። ሀገሪቱ ካሏት አመንዣጊ እንስሳት 34 ሚሊዮን የዳልጋ ከብት፣ 24 ሚሊዮን በግ፣ 18 ሚሊዮን ፍየልና 1.2 ሚሊዮን ግመል ይገኛሉ። ከሃገሪቱ አካባቢ ዳልጋ ከብት 70%፣ በግ 70%፣ ፍየል 30% ከደጋው አካባቢ ይገኛሉ። ቀሪው የዳልጋ ከብት በግና ፍየል እንዲሁም 100% ግመል በቆላውና አርብቶ አደሩ አካባቢ ይገኛሉ።

 

የሀገር ዝርያ ዳልጋ ከብት ልዩ ባህሪያት

1. በተለያዩ ምህዳር ቀጠናዎች የመላመድ ችሎታ

2. በሽታን የመቋቋም (የውስጥና የውጭ ጥገኞች) አቅም

3. ለተለያዩ ተግባራት ጠቃሚ ናቸው (ለግብርና፣ ለስጋና ለወተት)

4. ጥራቱ አነስተኛ በሆነ ተረፈ ምርት የሚቻለውን ምርት መስጠት

5. የውሃ እጥረትን የመቋቋም ችሎታ

 

በግራ በኩል የተመለከቱትን አገናኞችን/links በመጫን ስለተለያዩ የከብት ዝርያዎች ይወቁ፡፡

3.25
አማካይ: 3.3 (4 votes)
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation