Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

ስለባቄላ ምርት

ባቄላዎች የተሻለ ምርት እንዲሰጡ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት አስፈላጊ መረጃዎች ናቸዉ፦

የመሬትና የአፈር አዘገጃጀት፦

ባቄላዎች ከሎች ተክሎች አንፃር ብዙ አይመገቡም፡፡ ከ25-35 ኪግ ፎስፌት በሄክታር እና ከ75-80 ፖታሲየም በሄክታር በቂ ነዉ፡፡

እንደሌሎች ጥራጥሬዎች ናይትሮጂንን ከአየር ላይ ወስደዉ መለወጥ ስለሚችሉ የናይትሮጂን ማዳበሪያ አያስፈልጋቸዉም፡፡ ነገር ግን ናይትሮጂን መቀየር የሚችሉ ባክቴሪያዎች ያሉት አፈር ተመራጭ ነዉ፡፡

ትነሽ ብስባሽ ያለዉናደረቅ አፈር ለባቄላ ለስማሚ አይደለም፡፡ በመሆኑም ኮምፖስት ቢጨመርበት መልካም ነዉ፡፡

ለባቄላ ተክሎጩ መደገፊያ የሚሆን መቋምያ ከ1 ሜትር መብለጥ የለበትም፡፡

ባቄላን በዝራትና መንከባከብ፦

በየጊዜዉ አረም ማረም በጣም አስፈላጊ ነዉ፡፡ የመጀመሪያዉ አረም የማረም ስራ መሰራት ያለበት ከበቀለ ከ2-3 ሳምንታት በሗላ ነዉ፡፡

መሬቱ እርጥበታማ በሆነ ጊዜ መትከል በሽታን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ስንኮተኩተም በስሱ መሆን አለበት በተለይም በሚያብብበት ወቅት፡፡

በሽታን ለመከላከል ሰብልን አፈራርቆ መዝራት ያስፈልጋል፡፡

የባቄላን ምርት ለማሻሻል የሚያስችሉ ጥቆማዎች፦

በጭድና የታጨደ ሳር አፈሩን ማልበስ፡፡ ይህም እርጥበትን ለመያዝና አንዳንድ በሽታ አምጪ ዝምብን ለመከላል ይረዳል፡፡

ከሌሎች ሰብሎች ጋር እያቀላቀሉ መትከል፡፡ ልምሳሌ እንደ በቆሎ፣ ድንች፣ ኩከንበር፣ የመሳሰሉት፡፡ ምክንያቱም ለሌሎች ሰብሎች ናይትሮጂን ስለሚያበረክቱ፡፡

በየጊዜዉ አስፈላጊዉን መጠን ዉሃ ማጠጣት፡፡ በደረቅ ጊዜ መስኖ ሊያስፈልግ ይችላል፤ በመትከያና ጊዜና ከሱም አስር ቀናት በሗላ 35 ሚሜ በሳምንት፣ ከዛም በመቀጠል 50 ሚሜ በሳምንት፡፡

ተባይና በሽታን በሌሎች ጠቃሚ ማይክሮኦርጋኒዝሞች በመርጨት መከላከል ይቻላል፡፡

 

0
No votes yet
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation