Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

የወተት እንስሳት እርባታ

boys with zebu
የወተት እንስሳት አረባብና የወተት ተዋፅኦ አመራረትና አጠቃቀም ለተለያዩ ግልጋሎቶች ማለትም ለእርሻ ጉልበት፣ ለወተትና ለሥጋ የሚውሉ የተለያዩ ዝርያዎችን በመጠቀም በባህላዊ እና በዘመናዊ አያያዝ ከሌሎች የግብርና ሥራዎች ጋር በተጓዳኝና በጣምራ የሚሰራ ነው። የወተት እንስሳት አረባብ በአብዛኛው ባህላዊ ነው። ይሁን እንጂ ከ 40 ዓመታት በፊት የተሻሻሉ የውጭ ዝርያዎች በደጋውና በወይናደጋው ክልሎች ጊደሮችን፣ ኮርማዎችንና አባላዘር በመጠቀም ዘመናዊ የአረባብ ዘዴ እንዲስፋፋ ተሞክሯል። ዘመናዊ ዘዴዎችን ለማስፋፋት የጭላሎ እና የወላይታ እርሻ ልማት ድርጅቶች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
 
ከዚህም በተጨማሪ የሰው ሠራሽ ማዳቀያ ማዕከል ተቋቁሞ የተለያዩ ሰፋፊ የማራቢያ ጣቢያዎች አገልግሎት በመስጠት ዲቃላ ጊደሮች የሚሰራጩበት መንገድ ተከፍቷል። በደጋውና በወይናደጋው የወተትና የወተት ተዋፅኦ ያነጣጠረው በዳልጋ ከብት ላይ ነው። ይህም 88% የሀገሪቱ ህዝብ የሚኖርበት 70% የዳልጋ ከብት የያዘ ነው። በአርብቶ አደሩ ዘንድም ከዳለጋ ከብት፣ ከግመልና ከፍየል የሚመረተው ወተት የምግብ ምንጭና ዋስትና ነው። ይሁን እንጂ ዘመናዊ የእርባታ ዘዴው በአርብቶ አደሩ አካባቢ አልተስፋፋም። ይህም የሆነው ከፍተኛ ሀሩራማ የአየር ንብረት፣ የውሃ እጥረትና ተደጋጋሚ ድርቅ በመከሰቱ ነው።
በዚህ ክፍል ዉስጥ የሚከተሉትን ነገሮች እንመለከታለን፦
ስለእንስሳቱ ዝርያዎች
ስለአረባብና አስተዳደር
ስለከብቶች መዝገብ አያያዝ
ስለጥጃዎች አወላለድና እንክብካቤ
ስለከብት መኖ
ስለበሽታዎች
ስለእንስሳቱ ተዋፅዖዎች

 

2.454545
አማካይ: 2.5 (11 votes)
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation