Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

ስለልጆ ሰውነት ማሳወቅ

አንድ ልጅ የራሱ የሰውነት አካላት ምን እንደሚመስሉ እና ሰውነቱ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ ማወቅ አለበት፡፡ ይህንን እውቀት እንዲያዳብር የሚረዱ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ፡፡

  • ከልጅዎ ጋር መስታወት ፊት ቆመው የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን እየጠቆሙ ማሳየት
  • ልጅዎ ዓይኑን እንዲጨፍን ያደርጉና የሰውነት ክፍሎችን በመንካት በቃሉ እንዲጠራ ማድረግ
  • የራሱን ወይም የሌሎች ሰዎችን ቁመና የሚያሳዩ ስዕሎችን እንዲስል ማድረግ፤ የረሳቸው የሰውነት ክፍሎች ካሉ በጨዋታ መልክ ራሱ አስታውሶ እንዲጨምራቸው ማድረግ
  • ልጅዎን ወደፊት፣ ወደኋላ እና ወደጎን እንዲራመድና ወደታችና ወደላይ እንዲዘል መጠየቅ
  • ዕቃዎችን በመጠቀም ከሌሎች ዕቃዎች ጋር ያላቸውን የአቀማመጥ ግንኙነት ማሳየት (ከላይ፣ከታች ወይም ጎን ለጎን በማለት)

 

0
No votes yet
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation