Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

በዚህ ክፍል ዉስጥ

ዶክተርን ማየት (መጎብኘት)

የሕፃናት ስፔሻሊስት(ባለሞያ ዶክተር) አመራረጥ
ብዙ ጊዜ ለልጅዎ የሚሆን ዶክተር መምረጥ ያለብዎት ልጁ ከመወለዱ ከ3 ወር በፊት መሆን አለበት፡፡ ወዳጅዎችዎን ቤተሰብዎን ወይንም የእራስዎን ዶክተር እንዴት መምረጥ እንዳለብዎ ያማክሩ፡፡ ተገቢውን አማራጭ ካገኙ በኋላ ዶክተሩን ደውለው ቀጠሮ ይዘው ያናግሩት፡፡ ይህ ዶክተር በሕፃኑ ጤንነት ኃላፊነቱን ስለሚወስድ ለእርስዎና ለልጅዎ ተስማሚ የሆነ ዶክተር መሆኑን ያረጋግጡ፡፡

የዶክተር ክትትል
ሕፃኑን በየጊዜው ለዶክተሩ ማሳየት ይኖርብዎታል፡፡ ይህም ጤናማ እና ደስተኛ ሆኖ እንዲያድግ ይረዳዋል፡፡  አንድ ሕፃን በዶክተር መታየት ያለበት ጊዜ፡-

 1. በተወለደ በ24 ሰዓት ውስጥ
 2. ከተወለደ ከ 48 ሰዓታት በኋላ እና ወደ ቤት ከተመለሰ ከ2-4 ቀናት በኋላ
 3. በተወለደ 2-4 ሳምንታት ውስጥ
 4. በተወለደ በ2 ወሩ
 5. በተወለደ በ4 ወሩ
 6. በተወለደ በ6 ወሩ
 7. በተወለደ በ9 ወሩ
 8. በተወለደ በ12 ወሩ

በዶክተር ክትትል ጊዜ መታወቅ ያለባቸው ሁኔታዎች
በእያንዳንዱ የምርመራ ወቅት ዶክተሩ የልጁን ቁመት፣ ክብደት እና የጭንቅላቱን ሁኔታ ይመረምራል፡፡ ይህን የሚያደርገው የሕፃኑን የእድገት ሁኔታ ለመከታተል ነው፡፡ የህፃኑን ጭንቅላት፣ዓይን፣ጆሮ፣ሳምባ፣ልብ፣ከንፈር፣ወገብና ሆድ በሙሉ ዶክተሩ ይመረምራል፡፡ ልጅዎ እንደ እድሜው የደመነፍሳዊ እንቅስቃሴ (ሪፍሌክስ) መስማትና ማየት ችሎታውም ይታያል፡፡ ስለ ሕፃኑ የአስተዳደግ ሁኔታም ይጠይቅዎታል፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ ልጅዎ ቁጭ ማለት፣ መንከባለል እና መቆም መሞከር አለበት፡፡

 በሽታ የመከላከል አቅም (ክትባት)

ሌላው የሕፃኑ የምርመራ ሂደት ውስጥ የሚካተት ተደጋጋሚ በሽታ የመከላከል አቅሙን የሚያጠናክርበት ምርመራ ነው፡፡ ሕፃኑ እነዚህን ክትባቶች (በሽታ የመከላከል አቅሙን የሚያጠናክር መድኃኒት) እንዲወስድ ይደረጋል።  ይህም፡-

 • ለጉበት (ሂፕታይተስ ቢ)
 • ለ ዲፕቴሪያ፣ ፐርቱዲስ እና ቲታነስ
 • ለፖሊዮ
 • ለ ሚዝል፣ መምፕስን ሩቤላ (ሜሜአር)
 • ለሂሞፊሊያ ኢንፍሉኢንዛ ታይፕ ቢ (ሂፕ)
 • ቫርሴላ የጉድፍ (ባክሲን) ክትባት
 • ኒሞኒያ (ቫክሲን) ክትባት
1.5
አማካይ: 1.5 (4 votes)
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation