Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

በዚህ ክፍል ዉስጥ

ኮንዶሞች

Condoms

ስለ ኮንዶምን ብዙ ጊዜ የሚጠይቁ ጥያቄዎች

ኮንዶም ምንድን ነው?

ኮንዶም ማለት ቀጭን የሚለጠጥ ፕላስቲክ ሆኖ ለወንድ ልጅ ብልት እንዲበቃ ሆኖ የተሰራ የአባላዘር (እስፐርም) መቆጣጠርያ / ማጠራቀሚያ ከረጢት ነው፡፡ የኮንዶም አይነት ብዙ ነው፡፡ ይህ ሲባል በኮንዶሙ መጠን፣ ዓይነት እና ቀለም ሊለያይ ይችላል፡፡ አንድ ወንድ ከአንድ ሴት ጋር ግንኙነት ከመፈፀሙ በፊት በቆመው ብልት ላይ ኮንዶሙን ያጠልቃል፡፡ ኮንዶሙ የሚጠቅመው ወንዱ ልክ ዘሩን ሲረጭ ኮንዶም ዘሩን ይይዘውና ወደ ማህፀን ከመግባት ይከለክለዋል፡፡ ከጨረሰ በኋላ ኮንዶሙን በጥንቃቄ ከብልት ላይ ያወጣዋል፡፡ ይህ የሚሆነው ዘሩ ድንገት ወደ ሴቷ ብልት እንዳይፈስ ነው፡፡ ከዛም በኋላ ኮንዶሙ ይጣላል፡፡ ያረጁ ፣ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ ወይንም በኪስ ቦርሳ ውስጥ፣ በኪስ ውስጥ ወይንም ሞቃት ቦታ የተቀመጡ ኮንዶሞችን አይጠቀሙ፡፡

እውነት ኮንዶሞች ይሰራሉ?

አዎን እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ኮንዶሙን በትክክል ከተጠቀሙ  98 በመቶ እርግዝናን የመከላከል ብቃታ አለው፡፡ የዘር ፍሬን የሚገለው ኬሚካል ካለ ደግሞ 99 በመቶ የመከላከል ብቃት አለው፡፡ እንዲሁም ኮንዶም መጠቀም እርሶዎንና ጓደኛዎን በግብረስጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች እንደ ጨብጥ፣ ከርክር እና ኤች አይ ቪ ከመሳሰሉት ሊከላከልሎት ይችላል፡፡

  • ኮንዶሙ ላቴክስ ከተባለ ኬሚካል ካልተሰራ ከ ኤች አይ ቪ እና የመሳሰሉት በሽታዎች ላይከላከል ይችላል፡፡

ኮንዶሞችን የት ማግኘት እችላለሁ?

ኮንዶምን በሁሉም ሱቆችና የመድሃኒት መደብሮች በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያገኟቸው ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በአንዳንድ የቤተሰብ ክሊኒኮች ፣ ሆስፒታሎች የመሳሰሉት በነፃ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ሱቅ ወይንም መድሃኒት መደብር ሄዶ ኮንዶም ለመጠየቅ ምንም አይነት ይሉኝታ/ እፍረት  እንዳይሰማዎት ኮንዶም ሲጠይቁ ሀላፊነት የሚሰማው ሰው ስለሆኑ በዚያ ይኩሩ፡፡

እኔ ኮንዶምን ልጠቀም?

ኮንዶም ሲጠቀሙ  ከኤች አይ ቪ፣ እርግዝናና ሌሎች በሽታዎች ይከላከላል:: ነገር ግን ኮንዶም መጠቀም ከመጀመርዎ በፊት ለእርስዎ እንደሚሆንና እንደማየሆን ማወቅ አለበብወዎት ልክ እንደሌሎቹ  እርግዝና መከላከያ ዘይቤዎች ኮንዶም ለመጠቀም ዶክተር ማማከር አለብዎት፡፡

ኮንዶም መጠቀም ያለብዎት

  • ወደሌላ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ካለብዎት
  • ብዙ ጊዜ ግንኙነት የማይፈፅሙ ከሆነና ተደጋጋሚ የሆነ የእርግዝና መከላከያ መጠቀም የማይፈልጉ ከሆነ ነው፡፡

ላቴክስ የተባለውን ኬሚካል እርስዎ ወይም ጓደኛዎ አለርጂክ/ የማይስማማችሁ  ከሆነ ኮንዶም መጠቀም ትክክለኛ አማራጭ አይደለም፡፡

 

1.42857
አማካይ: 1.4 (7 votes)
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation