Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

ንብ እርባታ

የንብ እርባታ በአብዛኛው አርሶ አደር በተጓዳኝ የሚካሄድ የግብርና ንዑስ የሥራ መስክ ነው። ልማቱ የሚካሄደው ማርና ሰም ለመሰብሰብና ለመጠቀም ሲባል ነው። ማር ለመድሃኒትነት የሚውል ሲሆን ከሰሙ ተሸጦ ለገቢ ምንጭ ማዳበሪያነት ያገለግላል። ማርና ሰምን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ። ንቦች ማርና ሰም በማምረት በሚያደርጉት ጥረት ከእፅዋት ፈሳሽ፣ የአበባ ወለላ (ኔክታር) እና የፅጌ ብናኝ (ፖለን) እፅዋቶች እንዲራቡ ያደርጋል። በሃገራችን ብዙ የማር እፅዋት፣ አውራ ንቦች፣ በቂ ውሃና ለልማቱ መዳበር የሚስማማ የአየር ንብረትና የተፈጥሮ ቅንብሮች ይገኙበታል። በሀገራችን ከ10 ሚሊዮን በላይ አውራ ንቦች ይገኛሉ። 75% በባህላዊ፣በሽግግርና በባለፍሬም ቀፎ የሚራቡ ናቸው። በዓመት 28.5 ሺህ ቶን ያልተጣራ ማርና 3.2 ሺህ ቶን ሰም ይመረታል። ምርቱም ሀገሪቷ ካላት የተፈጥሮ ሀብት ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ ነው። ለዚህም ምክንያቶች፡-

  • ባህላዊ መንገድ መሆኑ
  • በማናብ በቂ እውቀትና ክህሎት አለመኖር
  • የግብርና ዘዴ በበቂ ሁኔታ አለመስፋፋት
  • የማናቢያ መሣሪያዎች እጥረትና ውድነት
  • የምርምር ተቋማት ውስንነት
  • የገበያና የብድር ሥርዓት አለመዘርጋት ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ከነዚህ ድረገፆች ማግኘት ይቻላል፦

 

3.5
አማካይ: 3.5 (2 votes)
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation