Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

ሞርጌጅ

የራስዎ የሆነ ቤት ባለቤት መሆን የግል ደህንነት ከመስጠቱም በላይ በህይወት ዘመንዎ የሚፈፅሙት ትልቁ ኢንቨስትመንት ነዉ፡፡ ቤት መግዛት በጣም ዉድ ነዉ፡፡ በመሆኑም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸዉ በአንድ ጊዜ ከፍለዉ የቤት ባለቤት የሚሆኑት፡፡ ለዚህም አይነተኛ መፍትሄ የሚሆነዉ ሞርጌጅ መዉሰድ ነዉ፡፡

ሞርጌጅ ማለት ቤት ለመግዛት የምንጠቀምበት የረጅም ጊዜ ብድር ሲሆን ብድሩ ተከፍሎ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቤቱ ለአበዳሪዉ እንደማስያዣ ያገለግላል፡፡ ክፍያዉም የሚፈፀመዉ በየወሩ አበዳሪዉና ተበዳሪዉ በተስማሙበት የገንዘብ መጠን ልክ ይሆናል፡፡ በእጅዎ ለቤት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ከሌሎት ሞርጌጅ አይነተኛ አማራጭ ነዉ፡፡

ብዙ ሰዎች ሞርጌጅ መዉሰድ ይፈራሉ፡፡ ቤትም መግዛት ከአቅማቸዉ በላይ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን አንድ ራስዎን መጠየቅ ያለቦት ለቤት ኪራይ የሚከፍሉት ገንዘብ ከሞርጌጅ ክፍያዎ እኩል ቢሆንስ? የአከራዮን ኪስ ከማበልፀግ ይልቅ የራስዎን ቤት በማግኘት ላይ ቢሰሩስ!

በዚህ ክፍል ሞርጌጅ ከየት እንደሚያገኙ፣ የሞርጌጅ አይነቶችን፣ የገዙት ቤት ትክክለኛ ዋጋን፣ እንዲሁም ሞርጌጅ ከገዙ በሗላ ያለቦትን ሀላፊነት በተመለከተ ለማሳየት እንሞክራለን፡፡

 

1
አማካይ: 1 (2 votes)
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation