Skip to Secondary Navigation Skip to Main Content

Current Domain

Ethiopiaለውጥ

Languages

በጀት አያያዝ

Writing a Check

 

 

እራስዎን ከብድር ነፃ ለማድረግም ሆነ ገንዘብ ለመቀቆጠብ አስበዉ ከሆነ በጀት መያዝ እና በበጀትዎ መንቀሳቀስ ቀላሉና ተመራጩ መንገድ ነዉ፡፡

ይህን ድህረ ገፅ ለማንበብ በመምጣትዎ የግል በጀትዎን ለማዘጋጀት የሚያስችልዎትን የመጀመሪያ እርምጃ ወስደዋል፡፡ ሊጠቀሙበት የሚችሉት የግል በጀት እንዲኖርዎት ለስኬታማ የግል በጀት የሚያስፈልጉትን ሶስት ቁልፍ ነጥቦች ልብ ይበሉ፡፡

1. ትክክለኛ እቅድ ያውጡ
 

በጀትዎ ውስጥ የሚያካትቷቸውን ወጪዎች መጠን ሲተምኑ ትክክለኛ ወጪዎችዎን የሚገልፅ ያድርጉ፡፡ ለምሳሌ ለመዝናናት በወር ከ 50 ብር በላይ እንደሚያጠፉ እያወቁ ለመዝናኛ ወጪ ብለው በወር የያዙት በጀት 10 ብር ከሆነ ጠቅላላ በጀትዎን ያቃውሰዋል፡፡ በተቻለዎት መጠን በጀትዎን ሲያዘጋጁ እውነተኛ ገቢና ወጪዎችዎን ይመዝግቡ፡፡

2. ገንዘብዎን በአግባቡ መቆጣጠር የሚችሉበትን መንገዶች ያመቻቹ
ገንዘብዎን መቆጠብ እና በአግባቡ መቆጣጠር የሚችሉባቸውን መንገዶች ይወቁ፡፡ በዚህ ማዕከል አንዳንድ ሊረዱዎት የሚችሉ ዘዴዎችን አካተናል፡፡

3. በጀትዎን ይጠብቁ
የግል በጀት አዘጋጁ ማለት በበጀት እየኖሩ ነው ማለት አይደለም፡፡ በጀቱን ማዘጋጀቱ የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃ ሲሆን ሚስጥሩ ባዘጋጁት በጀት መመራቱ ነው፡፡ በየወሩ በጀትዎን እና ወጪና ገቢዎን እያጣጣሙ መንቀሳቀስ አለብዎት፡፡

 

 

 

 

 

2.642855
አማካይ: 2.6 (14 votes)
እርስዎ የሚሰጡት ደረጃ: ማንም
© የቅጂ መብት 2001 - 2017 One Global Economy Corporation