በቀደሙት ክፍሎች እንደተገለፀው ለልጅዎ የትምህርት ስኬት የእርስዎ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ የልጆችዎን የቤት ሥራ መከታተልን እና ሲቸግራቸውም መርዳትን ይጨምራል፡፡ የእርስዎ የትምህርተ ደረጃ በቂ መስሎ ባይታይዎትም ልጆችዎን ሊረዱ የሚችሉባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ በእዚህ ክፍል ከጥቂቶቹ ጋር እናስተዋውቅዎታለን