|
ኤች አይ ቪ/ኤድስ
የመጀመሪያ የኤድስ ክስተት ብቅ ያለው 1974 አጋማሽ ላይ በአሜሪካን ኒውዮርክ ከተማ በሚኖሩ ጥቂት ግብረሰዶማውያን ላይ ነው፡፡ ለበሽታው መገኘት መንሥኤ የሆኑት ቀድሞ አዘውትሮ የማይታይ የካፖሊ ሳርኮማ (የካንሰር ጠባይ ያለው በውስጣዊ የአካል ክፍሎች ሁሉ የሚወጣ ለየት ያለ የኪንታሮት) በሽታ በ8 የኒውዮርከ ነዋሪ ወጣቶች ውስጥ መታየቱና በዚያው ሰሞን ከካፖሲስ ሳርኮማ በተጨማሪ በ "ፒ ሲ ፒ" (ሳንባን የሚያጠቃ የመተንፈስ በሽታ) የተያዙ ህሙማን በተለያዩ ከተሞችም መታየታቸው ነው፡፡ ቀድሞ የማይታወቀው ይህ የጤና ችግር የተከሰተባቸው ህሙማን ላይ ምርመራ ሲደረግ በተፈጥሮ ሊኖራቸው የሚገባ የበሽታ መከላከያ አቅም የተዳከመና የመነመነ ሆኖ በመገኘቱና እንዲህ ሊያመነምን የቻለበት መንሥኤው ምን እንደሆነ በዚያን ጊዜ ተለይቶ የታወቀ ስላልነበረ "ኤድስ የዘር ያልሆነ በሽታ የመከላከል ተፈጥሮ መመናመን አባዜዎች" በሚል ሀረግ የአፅሮት መጠሪያ ያገኘ ትልቅ የጤና ችግር ነው፡፡
|