» ቆሻሻን ባግባቡ ማስወገድ
ዙሪያችን ያለ ነገር በሙሉ አካባቢን ይወክላል፡፡ የሚኖሩበትና የሚሰሩበት መሬት፣ የሚተነፍሱት አየር፣ የሚጠጡት ውሃ እና የመሳሰሉት በአጠቃላይ አካባቢዎን ይወክላሉ፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የአካባቢ ብክለት ባለበት ቦታ ይኖራል፡፡ ይህን ስንል የቤት ውስጥ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ ወይም አፈር ተሸርሽሮ ለጎርፍ የሚዳርግበት ቦታን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ንፁህ በሚባል ቦታም ቢኖሩ አንድ አይነት ብክለትን ወይም በድርቅ ምክንያት የሚመጡ ችግሮችን እንዲሁም ጎርፍና የምድር ሙቀት (Global Warming) የሚያስከትሉትን ችግሮት ማምለጥ አይችሉም፡፡ በአጭሩ የከባቢ አየርና የውሃ ብክለት የመሳሰሉት ችግሮች በሆነ መልኩ ተፅእኖ ያሳድርብዎታል፡፡ማንኛውም ሰው ቆሻሻን በተገቢው መንገድ በማስወገድም ሆነ ድጋሚ ማገልገል የሚችሉ ነገሮችን ጥቅም ላይ በማዋል የአካባቢን ብክለት መታገድ ይችላል፡፡